Skip to main content

Amharic - The Lightning and the Thunder

Page 1

መብረቅ እና ነጎድጓድ ለዝናብም ትእዛዝን፥ ለነጎድጓድም መብረቅ መንገድን ባደረገ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ አይቶ ገለጠው፥ አዘጋጀውም፥ መረመረውም። ለሰውም፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው አለ። ኢዮብ 28:26-28

ፔንታቱች ሙሴም በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጎድጓድና በረዶ ላከ፥ እሳትም በምድር ላይ ፈሰሰ፤ እግዚአብሔርም በግብፅ ምድር ላይ በረዶ አዘነበ። እግዚአብሔር ሆይ፤ (በቂ ነውና)፤ ከእንግዲህ ወዲህ ኃይለኛ ነጎድጓድና በረዶ እንዳይወርድ፤ እለቅቃችኋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትቆዩም። ሙሴም፦ ከከተማ እንደወጣሁ እጄን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፤ ነጎድጓዱም ይቆማል፥ በረዶም ከእንግዲህ አይሆንም፤ ምድሪቱም የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ አለው። ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፥ እጁንም ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጎድጓዱና በረዶውም ቆመ፥ ዝናቡም በምድር ላይ አልፈሰሰም። ፈርዖንም ዝናቡና በረዶው ነጎድጓዱም እንደቆመ ባየ ጊዜ ኃጢአቱን ጨመረ፥ እርሱና አገልጋዮቹም ልባቸውን አደነደኑ። ዘጸአት 9 :23፣28-29፣33-34 በሦስተኛው ቀን በማለዳ ነጎድጓድና መብረቅ፣ ከባድ ደመና በተራራው ላይ ሆነ፣ እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ ነበር፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። ዘጸአት 19:16 ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቅን፥ የቀንደ መለከቱንም ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ባዩ ጊዜ ተንቀጠቀጡና ርቀው ቆሙ። ዘጸአት 20:18

ታሪክ የእግዚአብሔር ጠላቶች ይደቅቃሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር የምድርን ዳርቻ ይፈርዳል፤ ለንጉሡም ኃይል ይሰጣል፥ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል። 1ኛ ሳሙኤል 2:10 ሳሙኤልም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሲያቀርብ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀን በፍልስጥኤማውያን ላይ በታላቅ ነጎድጓድ አንጐደጐደ፥ አስደነገጣቸውም፥ በእስራኤልም ፊት ተመቱ። 1ኛ ሳሙኤል 7:10


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Amharic - The Lightning and the Thunder by Filipino Tracts and Literature Society Inc. - Issuu